የኢትዮጵያ ፖስታ የታዳጊዎችን የደብዳቤ ፅሁፍ ውድድር በደማቅ ሁኔታ አጠናቋል።

አለም አቀፍ የሙዚየም ቀን አከባበርን በማስቀጠል የኢትዮጵያ ፖስታ የታዳጊዎችን የደብዳቤ ፅሁፍ ውድድር የመዝጊያ ዝግጅት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። በውድድሩ ተሳትፈው ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ ታዳጊዎች የኢትዮጵያፖስታ የታብሌት ሽልማት አበርክቷል። ይህ ዝግጅት ተስፋቸውን እና ህልማቸውን የሚገልጹ ወጣት ተሰጥኦዎችን ጊዜ በማይሽረው የደብዳቤ ጽሑፍ ጥበብ አጉልቶ ያሳየ ነበር።  “ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ እናግኝ” በሚል ርዕስ የተካሄደው ውድድር ይህን ዘርፈ ብዙ ችግር መፍታት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል።

በዝግጅቱ ላይ ዋና ኮሜርሻል ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በኢትዮጵያ ፖስታ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ ለታዳሚዎች ገለፃ በማድረግ ለፈጠራ እና ለደንበኞች እርካታ ያለንን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።  በተጨማሪም የፖስታ ሙዚየም ሱፐርቫይዘር አቶ ደረጀ ሁሉንም ታዳሚ የኢትዮጵያፖስታ ሙዚየምን አስጎብኝተዋል።

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ የኢ-ኮሜርስ ዲጂታል የገበያ ማዕከልን ለማቅረብ ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና ከሲኤስኤም አፍሪኮም ጋር በጋራ ተፈራርሟል።

በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ዲጂታል የገበያ እድል ለመፍጠር የተዘጋጀው ፕሮጀክት፥ በዛሬው እለት ለየኢትዮጵያ ፖስታ የኢ-ኮሜርስ ዲጂታል የገበያ ማእከልን ለማቅረብ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና ሲ.ኤስ.ኤም ከአፍሪኮም ጋር በጋራ በመሆን ተፈራርመዋል።

Read More »