ሳሚ ጣፋጭ አይወድም። ግን አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ሲወጣ በር ላይ ትልልቅ ተማሪዎች ጀላቲ ገዝተው ሲበሉ አየ። ጣፋጭ ባይወድም ቢጫ፣ ብርቱካንማ፣ አረንጓዴ ጀላቲዎቹን መቅመስ ፈለገ። ሲቀምሰውም ራሱ ጀላቲ መስራት ፈለገ። ጀላቲ ለመስራት የሚያስፈልጉት ለስላሳ፣ ፍሪጅ፣ እናም ሌሎች ነገሮች የሉትም። ግን ሳሚ ‘ይህን ጀላቲ እሰራዋለሁ!’ አለ።
በ‘በርት አዋርድ ፎር አፍሪካን ሊትሬቸር’ ተሸላሚ ደራሲና ፀሐፊ ሊንዳ ዮሐንስ፣ ለራሷ አራት ትንንሽ ልጆች እንዲሁም ለመላ የኢትዮጵያ ልጆች የቀረበው ‘እሰራዋለሁ!’፣ ህጻናት ችግር ፈቺነትና የፈለጉትን ነገር ለማግኘት ስለመጣጣር እንዲማሩና ከእነሱም ጋር እነኚህን የህይወት ክህሎቶች አንስቶ ለመነጋገር መልካም እድልን ይፈጥራል።
Additional information
Language: Amharic
Pages: 12
Ages: 4-8
Publication year: 2016 (Ethiopian calendar)
Reviews
There are no reviews yet.