የኢትዮጵያ ፖስታ የስራ ላይ ልምምድ ሲያደርጉ ለነበሩ አዲስ ተመራቂ ተማሪዎች በሰርተፊኬት እውቅና ሰቷል።

በፋይናንስ፣ በሰው ሃይል አስተዳደር፣ በደንበኛ አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች የስራ ክፍሎች ውስጥ ተመድበው ሲሠሩ የነበሩ ተማሪዎችን ለ 2 ወራት በቆየ የስራ ላይ ልምምድ በማሰማራት ስለ ስራው በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው አድርጓል።