የኢትዮጵያ ፖስታ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

የስምምነቱ ዋና አላማ የመንገድ ፈንድ እድሳትን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የአገልግሎት መስጫ ቅርንጫፎች እና በዓመታዊ የተሽከርካሪ ቴክኒክ ደህንነት ምርመራ ተቋማት እንዲኖር ማድረግ ሲሆን ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ቦታ መስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።