ኢትዮጵያን የአፍሪካ የፖስታ ጥቅሎች እና የኢ-ንግድ ዕቃዎች የሎጅስቲክስ ማዕከል ለማድረግ ያለመው ታላቅ አህጉራዊ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ!

በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) እና በኢትዮጵያ ፖስታ ትብብር የተዘጋጀው “የአፍሪካ ቀጠናዊ የትራንስፖርት አውደ ጥናት” ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ የፖስታ እና የአቪዬሽን ተቋማት አመራሮችን በማሰባሰብ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።