በኢትዮጵያ ፖስታ እና በኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ሃውስ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ::

በኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና በኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ሃውስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኤልያብ ጌታቸው የተፈረመው ይህ የአጋርነት ሰነድ የቤት ለቤት መልእክቶችን እና ሌሎች የመልዕክት ልውውጥ አገልግሎቶችን ለደንበኞች ለማድረስ የሚያስችል ነው።