በኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና በኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ሃውስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኤልያብ ጌታቸው የተፈረመው ይህ የአጋርነት ሰነድ የቤት ለቤት መልእክቶችን እና ሌሎች የመልዕክት ልውውጥ አገልግሎቶችን ለደንበኞች ለማድረስ የሚያስችል ነው። የኢትዮጵያ ፖስታ ባሉት 700 የሃገር ውስጥ ቅርንጫፍ ፖስታ ቤቶች የበሽ ገበያ እንዲሁም በትልቅ የሎጅስቲክስ አቅም የሚጓጓዙ የኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ሃውስ ምርቶችን በሃገር ውስጥ እንዲሁም በተለያዩ የውጪ ሃገራት ለሚገኙ ደንበኞች ማድረስን ያካትታል።

News
የኢትዮጵያ ፖስታ የ9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረበ።
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የ2018 በጀት ዓመት የ 9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቦ አስገመገመ።








