የኢትዮጵያ ፖስታ እና ኦሮሚያ ጤና ቢሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ላይ ያተኮረ ስትራቴጂያዊ ውይይት አደረጉ።

የኢትዮጵያ ፖስታ  ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመገናኘት በክልሉ የሚገኙ የጤና ናሙና ሎጂስቲክስ፣ የፋይናንሺያል እና የመልዕክት አገልግሎቶችን በቅንጅት መስጠት ላይ ያተኮረ የትብብር ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሂዷል።