የኢትዮጵያ ፖስታ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር የመገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ቢረዳ እንዲሁም የንብረት አስተዳደር ክፍል ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ይፍቱስራ መኮንን መገልገያ ቁሳቁሶቹን ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ያስረከቡ ሲሆን የመቄዶኒያ አረጋዉያን የቡራኬ ስነስርዓት አድርገዋል።