የኢትዮጵያ ፖስታ የአየር ኃይላችንን 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ያዘጋጃቸውን አራት አይነት ታሪካዊ ቴምብሮች በይፋ አስመርቋል።

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሰረተበትን 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አክብሯል። የኢትዮጵያ ፖስታ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ ለመዘከር ያሳተማቸውን አራት አይነት ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፋ አስመርቋል።