የኢትዮጵያ ፖስታ የአየር ኃይላችንን 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ያዘጋጃቸውን አራት አይነት ታሪካዊ ቴምብሮች በይፋ አስመርቋል።

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሰረተበትን 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አክብሯል። የኢትዮጵያ ፖስታ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ ለመዘከር ያሳተማቸውን አራት አይነት ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፋ አስመርቋል።

የመከላከያ ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ፖስታ የአገራችንን ታሪክና አኩሪ ገጽታ ለቀጣዩ ትውልድም ሆነ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የቆየ ልምድ አለው። እነዚህ ቴምብሮች የአየር ኃይሉን የ90 ዓመት የጥንካሬና የኩራት ጉዞ የሚዘክሩ ናቸው።

ታሪክን በቴምብር ሰንደን ለትውልድ እናስተላልፋለን!

መልካም 90ኛ ዓመት ለጀግናው አየር ኃይላችን!

More updates Ethiopost

News

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፉ አስመረቀች።

የኢትዮጵያ ፖስታ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ታሪካዊ እሴቶቻችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ይህንን ታላቅ ኩነት አስመልክቶ የወጣው ልዩ የመታሰቢያ ቴምብርም ተቋማችን የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ስኬት ለዓለም በማብሰር ረገድ ያለውን ሚና የሚያጎላ ነው።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ኩባንያ “ልባም” የተሰኘውን የዲጂታል የህይወት መድን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ተሸላሚ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲያረጋግጥ፣ ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

Read More »
News

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በአሐዱ ባንክ መካከል በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ በአገልግሎት ማስፋፋት እና በፋይናንስ ዘርፍ የሚደረጉ ትብብሮችን በማጠናከር ለህብረተሰቡ የቀረበ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለማቅረብ እየሠራ ባለው ሥራ ላይ ይህ የስምምነት ፊርማ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

Read More »