የአለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) ከፍተኛ አመራሮች ከኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር ውይይት አካሄዱ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ከዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተገናኝተው የተቋሙን የለውጥ እና የዘመናዊነት ጉዞ አስመልክቶ ውይይት አካሂደዋል።