ወደ አራዳ ፖስታ ቤት የተዘዋወረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም በይፋ ተመረቀ!

ዛሬ መስከረም 29፣ 2019 ዓ.ም ወደ አራዳ ፖስታ ቤት የተዘዋወረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም በይፋ ተመረቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ላለፉት 50 አመታት በዋናው መስሪያ ቤት ሲገለገልበት የቆየውን የፖስታ ሙዚየም በዘመናዊ መልክ በታደሰው እና በታሪካዊነቱ በሚታወቀው አራዳ ፖስታ ቤት ተዘዋውሮ ዛሬ በይፋ ስራውን ጀምሯል። ይህ ታሪካዊ ሙዚየም የረጅም ጊዜ የፖስታ ታሪካችንን፣ ቴምብሮችን እና ቅርሶችን በውስጡ በመያዝ […]
የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ፖስታ የቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያሥላሴ ወደ ታሪካዊው አራዳ ፖስታ ቤት የተዘዋወረውን እንዲሁም በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቆ ሥራ የጀመረውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ጎበኙ።

በጉብኝታቸው ወቅት ለ50 ዓመታት በዋናው መሥሪያ ቤት ተጠብቀው ቆይተው በዘመናዊ መልክ የተደራጁ ብርቅዬ ቴምብሮችንና ታሪካዊ የፖስታ ቅርሶችን በመመልከት በአደረጃጀቱ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።