ክብርት ሚኒስትር እና የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሐና አርዓያሥላሴ በስፍራው ሲደርሱ በኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በጉብኝታቸው ወቅት ላለፉት 50 ዓመታት በዋናው መሥሪያ ቤት ተጠብቀው የቆዩትን እና አሁን በዘመናዊ መልኩ በታደሰው የአራዳ ፖስታ ቤት ውስጥ የተደራጁትን የሀገራችንን የረጅም ጊዜ የፖስታ ጉዞ የሚያስረዱ ብርቅዬ ቴምብሮችና ታሪካዊ ቅርሶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያሥላሴ በሙዚየሙ ውስጥ ባዩት የታሪክና የቅርስ አደረጃጀት የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።
አክለውም ተቋሙ የሀገራችንን የፖስታ ታሪክና ቅርስ ለተከታታዩ ትውልድ የሚያስተላልፍ አበይት የማዕከል ሚና እንዳለው በመጠቆም፣ በሙዚየም ልማት ላይ የሚሰሩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ተቋሙ በሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ዘንድ እንዲጎበኝ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።











