የኢትዮጵያ ፖስታ ለአገልግሎት ማሻሻያ የሚሆኑ ዘመናዊ ላፕቶፖችን ከIOM ተረከበ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ከIOM ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ እና ለቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ማጠናከሪያ የሚውሉ ዘመናዊ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ተረክቧል። የኢትዮጵያ ፖስታን በመወከል የቴክኖሎጂ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኢብራሒም ከድር የስምምነት ሰነዱን እና የቁሳቁስ መረከቢያ ቅጹን የተፈራረሙ ሲሆን፣ የ26ቱ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ርክክብም ተፈጽሟል፡፡ ይህ ድጋፍ IOM ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም […]