የኢትዮጵያ ፖስታ ለአገልግሎት ማሻሻያ የሚሆኑ ዘመናዊ ላፕቶፖችን ከIOM ተረከበ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ከIOM ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ እና ለቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ማጠናከሪያ የሚውሉ ዘመናዊ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ተረክቧል። የኢትዮጵያ ፖስታን በመወከል የቴክኖሎጂ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኢብራሒም ከድር የስምምነት ሰነዱን እና የቁሳቁስ መረከቢያ ቅጹን የተፈራረሙ ሲሆን፣ የ26ቱ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ርክክብም ተፈጽሟል፡፡
 
ይህ ድጋፍ IOM ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የሚያካሂደውን የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ የማስፋፋት ስራ የሚያግዝ ነው። የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ቅርንጫፎቹ በኩል የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ፣ የባዮሜትሪክ መረጃ ስብሰባ፣ የካርድ ህትመት እና ስርጭት ስራዎችን በዋነኝነት የሚያከናውን በመሆኑ፣ የአገልግሎት ጥራትንና ፍጥነትን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ ተብሏል።
 
በተያያዘም ይህ አጋርነት የኢትዮጵያ ፖስታን የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት በማጠናከር የተሳለጠ የዲጂታል አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግቦች ለማሳካት የተደረገ ጠቃሚ እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ስልጠናው ለዲስትሪክት አመራሮችና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፣ የስልጠና ምስክር ወረቀትም ተበርክቷል። ተሳታፊዎች ያገኙትን እውቀት በየዲስትሪክታቸው በመተግበር አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ በብቃት ለማድረስ ተስማምተዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን በሀገረ አቀፍ ደረጃ ለማስፋፋት የሚያስችለውን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ። 

የስልጠናው ዓላማ የአገልግሎቱን አሰራር፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የደንበኛ አገልግሎት አቅም ማሻሻል ነው። ይህም አገልግሎቱን በሁሉም የፖስታ ቅርንጫፎች በብቃት ለማስፋፋት ይረዳል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለአገልግሎት ማሻሻያ የሚሆኑ ዘመናዊ ላፕቶፖችን ከIOM ተረከበ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ከIOM ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ እና ለቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ማጠናከሪያ የሚውሉ ዘመናዊ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ተረክቧል። የኢትዮጵያ ፖስታን በመወከል

Read More »
News

የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ፖስታ የቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያሥላሴ ወደ ታሪካዊው አራዳ ፖስታ ቤት የተዘዋወረውን እንዲሁም በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቆ ሥራ የጀመረውን  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ጎበኙ።

በጉብኝታቸው ወቅት ለ50 ዓመታት በዋናው መሥሪያ ቤት ተጠብቀው ቆይተው በዘመናዊ መልክ የተደራጁ ብርቅዬ ቴምብሮችንና ታሪካዊ የፖስታ ቅርሶችን በመመልከት በአደረጃጀቱ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።

Read More »