የኢትዮጵያ ፖስታ በአዲሱ የ”PROPEL” ስትራቴጂ ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

መድረኩ የተቋሙን ራዕይ በተቀናጀ ስትራቴጂና ወጥ በሆነ አሰራር ለማሳካት እንዲሁም አፈጻጸምን እና ሀገራዊ ፋይዳን ለማሳደግ የጋራ ግንዛቤ የሚፈጠርበት ነው።
የኢትዮጵያ ፖስታ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ስልጠናው ለዲስትሪክት አመራሮችና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፣ የስልጠና ምስክር ወረቀትም ተበርክቷል። ተሳታፊዎች ያገኙትን እውቀት በየዲስትሪክታቸው በመተግበር አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ በብቃት ለማድረስ ተስማምተዋል።