የኢትዮጵያ ፖስታ እና የሩሲያው የኢ-ኮሜርስ ኩባንያ ‘RWB’ ከፍተኛ አመራሮች የገቢና ወጪ ንግዱን ማቀላጠፍ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያዩ፡፡

ቀደም ሲል የተፈረመውን የአጋርነት ስምምነት ተከትሎ በተካሄደው በዚህ ምክክር፣ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያለውን ዓለም አቀፍ የኢ-ኮሜርስ የገቢና ወጪ ንግድ ሂደት ተግዳሮቶች ለመቅረፍና አገልግሎቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ በሚቻልባቸው አሠራሮች ላይ ትኩረት ተደርጓል።
በቻይና ፖስታ ቢሮ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሊዮ ጂንሮንግ የተመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፖስታ የሥራ ውይይት እና ጉብኝት አደረገ፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ ፖስታ ያለውን ሰፊ መሠረተ ልማትና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያለውን አጋርነት በመጠቀም አዲስ አበባን የምሥራቅ አፍሪካ የኢ-ኮሜርስ ማዕከል ለማድረግና በዲጂታል አሠራርና በአቅም ግንባታ በጋራ ለመሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል።