የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከሩሲያው ግዙፍ የኢ-ኮሜርስ ኩባንያ ‘RWB’ ልዑካን ቡድን ጋር በዛሬው ዕለት በሥራ ላይ የሚገኘውን የኢ-ኮሜርስ የገቢና ወጪ ንግድ ይበልጥ ማቀላጠፍ በሚቻልባቸው አስቻይ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።
መቀመጫውን ሩሲያ ያደረገው ‘RWB’ ኩባንያ ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) አስተባባሪነት ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ፖስታ ተገኝተው ከዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና ከከፍተኛ አመራሮች ጋር መክረው እንዲሁም የተቋሙን ቅርንጫፎችና የኢ-ኮሜርስ መጋዘኖች በመጎብኘት በጋራ ለመሥራት የሚያስችሉ የአጋርነት ስምምነት መፈረማቸው የሚታወስ ነው።
በዛሬው ምክክርም በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የኢ-ኮሜርስ የገቢና ወጪ ንግድ ሂደት ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እንዲሁም የንግድ እንቅስቃሴውን ይበልጥ ቀልጣፋ እና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ አሠራሮችን ማመቻቸትና ማጠናከር በሚቻልባቸው ቁልፍ ነጥቦች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ ፖስታ













