በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁጥር-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የግብር ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ ፖስታ አመራሮችና ሠራተኞች በሁለት ዙር ሲሰጡት የቆዩት የግብር ሕግና አሰራር ስልጠና ተጠናቋል።
በስልጠናው መዝጊያ መርሃ-ግብር ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ የሥልጠና ክፍል ኃላፊ ዶ/ር እንዳልካቸው አበበ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ ስልጠናው በተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ዘንድ በታክስ ሕግና አሰራር ዙሪያ የነበራቸውን ግንዛቤ ያጎለበተ ወሳኝ መድረክ እንደነበር ገልፀው፣ ሰልጣኞች በሁለቱም ዙሮች ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር እንዲለውጡ አሳስበዋል።
የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የግብር ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ተግባሩ ታምሩ በበኩላቸው፤ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ግብር ከፋዮች በመሰረታዊ የግብር ሕጎችና አሰራሮች ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ ግብርን በፍቃደኝነት የመክፈል ባህል እንዲዳብርና ባለማወቅ የሚከሰቱ ቅጣቶችን ለማስቀረት አልሞ የጀመረውን ስልጠና በስኬት ማጠናቀቁን ገልፀዋል።
ይህ ስልጠና በመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር ቀጥተኛ ከሆኑ የግብር አይነቶች በተለይም ከቅጥር የሚገኝ ገቢ፣ የወጪ መጋራት እና ሌሎች መሰረታዊ የታክስ አሰራሮች ላይ ትኩረት አድርጎ የተሰጠ ሲሆን፣ ሰልጣኞችም በቆይታቸው በቂ ግንዛቤ መጨበጣቸውን ገልፀዋል።

ወደ አራዳ ፖስታ ቤት የተዘዋወረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም በይፋ ተመረቀ!
ዛሬ መስከረም 29፣ 2019 ዓ.ም ወደ አራዳ ፖስታ ቤት የተዘዋወረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም በይፋ ተመረቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ላለፉት 50 አመታት በዋናው መስሪያ ቤት












