ይህ ዕውቅና የኢትዮጵያ ፖስታን አሰራር ወደ ላቀ የቴክኖሎጂ ደረጃ ለማሸጋገር የተደረገውን ያልተቋረጠ ጥረት የሚያንፀባርቅ ነው። በተለይም ላለፉት አምስት ዓመታት ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶ ካስመዘገባቸው ዋና ዋና ስኬቶች መካከል፡-
የብሔራዊ መታወቂያ ትስስር ፡ ብሔራዊ መታወቂያን ከተቋሙ የተለያዩ አገልግሎቶች ጋር በማስተሳሰር ይበልጥ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ዘመናዊ አሰራር መዘረጋቱ፤
ዘመናዊ ክትትል (Real-time Monitoring)፡ ደንበኞች መልእክቶቻቸውን ባሉበት ሆነው በቀላሉ መከታተል የሚችሉበት የዲጂታል ስርዓት ተግባራዊ መደረጉ፤
የተሻሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ ፡ የፖስታ እና የሎጅስቲክስ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በማገዝ ይበልጥ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ ማድረግ መቻሉ ተቋሙን ለዚህ ትልቅ ስኬት አብቅቶታል።
ኢትዮጵያ ፖስታ ለተሰጠው እውቅና ልባዊ ምስጋናውን እያቀረበ፤ ይህ ዕውቅና ለተቋሙ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ሲሆን፣ ወደፊትም የ “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ሀገራዊ ስትራቴጂን እና ራዕይን ለማሳካት የበኩሉን ከፍተኛ ድርሻ ከመወጣት ባለፈ፣ የላቀ፣ ፈጣንና ደህንነቱ የተጠበቀ ዘመናዊ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለማቅረብ በትጋት መስራቱን ይቀጥላል።







