የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ላለፉት ተከታታይ አመታት በተሰሩት የሪፎርም ስራዎች ላይ ተመስርቶ ‹‹በጥልቀት እና በስፋት›› በሚል ስትራቴጂክ ፕላን ተቋሙን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ ያለው ስራ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም በተሰራው ሪፎርም ላይ ተንተርሶ በመጡት ለውጦች ምክንያት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ የመስራት እድሎች እየፈጠረ እንደሚገኝ እና ከዓለም የፖስታ አገልግሎቶች የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ ሽልማቶችን የተቀበለበት ሁኔታ እንዳለ አብራርተዋል፡፡
አቶ ዳግማዊ ቴክኖሎጂውን በሚገባ ከመጠቀም እና ተደራሽነትን ከማስፋት አንጻር የኢትዮጵያ ፖስታ በቅርቡ ዝግጅታቸውን አጠናቆ ወደ ስራ ሊያስገባቸው ያቀዳቸውን የኢ-ኮሜርስ መተግበሪያ እና የቨርቹዋል ፖስታ አገልግሎቶች በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በተያያዘም አገልግሎቶቹ በሚወጡበት ጊዜ ከምንም በላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ለደንበኞቹ ቅርብ የሚሆንበትን አሰራር ለመዘርጋት የሚያስችል እንደሆነም ገልጸዋል፡፡