የኢትዮጵያ ፖስታ ከሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት በተሰጠው ውክልና መሰረት የውል ጽሁፎችን በማሰናዳት እናንተን ለማገልገል ከዛሬ ሐምሌ 1 ፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተመረጡ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ጀምራል።
የምንሰጠው አገልግሎት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት የሚቀርቡ
✅ የውክልና ስልጣን ምዝገባ
✅ የብድር ውል ምዝገባ
✅ የንብረት ሽያጭ ውል ምዝገባ
✅ የሊዝ ውል ምዝገባ
✅ የንብረት ልገሳ ውል ምዝገባ
✅ የውጭ ሰነዶች ምዝገባ እንዲሁም በ ውጪ ጉዳይ የተረጋገጡ የውጭ ሰነዶች ምዝገባ ውሎች
በዛሬው እለት የተጀመረውን አገልግሎታችንን በዋናው ፖስታ ቤት፣ በልደታ ቅርንጫፍ፣ ቦሌ መድኃኒአለም ቅርንጫፍ፣ አራት ኪሎ ቅርንጫፍ እና በቤተል ቅርንጫፎቻችን ማግኘት እንደምትችሉ እንገልጻለን፡፡
በልህቀት ልናገለግልዎ ዝግጁ ነን!!