የአለም የፖስታ ቀን ዘንድሮ መስከረም 29 /2017 ለ55ኛ ጊዜ ”ለ150 ዓመታት የዘለቀ ግንኙነት እና በአለም ዙሪያ ያሉ ሕዝቦችን ማጎልበት” በሚል መሪ ቃል በመላው አለም እየተከበረ ይገኛል።
እ.ኤ.አ በ1874 ዓ.ም የተመሠረተው ዓለም አቀፍ የፖስታ ህብረት የተሰኘው ተቋም ምስረታው የተደረገው የሲውዘርላንድ ዋና ከተማ በሆነችው በርን ላይ ነው። ህብረቱ በቁጥር 195 የሚሆኑ አባል አገራት ያሉት ሲሆን ከእነርሱም መካከል ኢትዮጵያ አንዷ በመሆን እ.ኤ.አ.1908ዓ.ም. ተቀላቅላለች። ዓለም አቀፍ የፖስታ ህብረት ከተመሰረተ 150ኛ ዓመቱን ከአለም የፖስታ ቀን ጋር ታሳቢ በማድረግ የኢትዮጵያ ፖስታ ይህንን ታሪካዊ ቀን በማክበር ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬ ይህንን ታላቅ ቀን በአለም ዙሪያ ካሉ ወገኖቻችን እና ከእኛ ጋር ለማክበር ትውልድ የተሻገረ የወዳጅነት ታሪክን ይጎብኙ።

News
የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲቱት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
ይህ አጋርነት ዘመናዊ የካርታ አሰራርን በኢትዮጵያ ፖስታ ሎጅስቲክስ ማዕቀፍ ውስጥ በማካተት የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን እና ጥራትን ለማሳደግ ያለመ ነው:: ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ፈጣን እና አስተማማኝ የቤት ለቤት እደላ አገልግሎትን በማሳለጥ የደንበኞችን እርካታን ማሻሻል ይቻላል።