የኢትዮጵያ ፖስታ የ2017 በጀት አመት አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት አመት እቅድ ውይይት አካሄደ።

ለሁለት ቀናት በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም በድርጅቱ የስትራቴጂክ ምሰሶዎች ላይ ተመስርቶ የቀረበ ሪፖርት እና የቀጣይ በጀት አመት እቅዶች በስፋት የተቃኙበት ነበር። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም የተመዘገበበት እንደሆነ የተነሳ ሲሆን እንደተቋም በቀጣይ ትኩረት ሊሰጥባቸው ይገባል ተብለው በዝርዝር የቀረቡ ጉዳዮች ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡

በቀርቡት ሪፖርቶች መሰረት ሊስተካከሉ እና ሊጠናከሩ ይገባቸዋል የተባሉ የስራ ማዕቀፎች ላይ ያተኮሩ ገለጻዎች የተካተቱ ሲሆን እርምት ይፈልጋሉ በተባሉ ነጥቦች ላይም ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል። በቀጣይም የ2018 በጀት ዓመት ሊሰሩባቸው በታሰቡ እቅዶች ላይ ጥልቅ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በመድረኩ ላይ በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶች የዋንጫ፣ የሜዳሊያ እና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በውይይቱ መጠናቀቂያ ላይም የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እንደ ተቋም ለተቀመጠው የ2018 በጀት ዓመት እቅድ በአዲስ ጉልበት እና መነሳሳት ራዕያችንን በትጋት ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል። የኢትዮጵያ ፖስታ ከታለመለት ከፍታ ላይ ለማድረስ ከሁሉም የድርጅቱ ሰራተኞች ትጋት እና አገልጋይነት የሚጠበቅ መሆኑን ገልፀዋል።

More updates Ethiopost

News

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በእልባት ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውል ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ፖስታን በመወከል ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር እና  በእልባት ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን በኩል ደግሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ነፃነት ራያ  ተፈራርመዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢት-ስዊች አክሲዮን ማሕበር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

በስምምነት ፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ እና ኢትስዊች አክሲዮን ማሕበር የተፈራረሙት ስምምነት የኤጀንት ኔትወርክ ማኔጅመንት መተግበሪያን በጋራ ለማበልፀግ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ነባር የቦርድ አባላት የሽኝት እና ለአዲሱ ቦርድ አባላት የአቀባበል ስነስርአት ተካሄደ።

በሽኝት ሥነሥርዓቱ ላይ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ የተቋሙ የስትራቴጂ እቅድ ግቡን እንዲመታ የቦርድ አባላቱ ያበረከቱትን ጉልህ አስተዋፅኦ በማንሳት በኢትዮጵያ ፖስታ ውስጥ ትልቁን ታሪክ እንደፃፉ እና ትልቅ ምስጋና እና ክብር እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

Read More »