የኢትዮጵያ ፖስታ ነባር የቦርድ አባላት የሽኝት እና ለአዲሱ ቦርድ አባላት የአቀባበል ስነስርአት ተካሄደ።

ላለፉት ሶስት ዓመታት የኢትዮጵያ ፖስታን ሲያገለግል የነበረው ቦርድ አመራሮች እና አባላት የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ በተገኙበት በስካይ ላይት ሆቴል በታላቅ ክብር ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

በሽኝት ሥነሥርዓቱ ላይ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ የተቋሙ የስትራቴጂ እቅድ ግቡን እንዲመታ የቦርድ አባላቱ ያበረከቱትን ጉልህ አስተዋፅኦ በማንሳት በኢትዮጵያ ፖስታ ውስጥ ትልቁን ታሪክ እንደፃፉ እና ትልቅ ምስጋና እና ክብር እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

እንዲሁም በዚሁ እለት አዲሱ የኢትዮጵያ ፖስታ የቦርድ አባላት በእለቱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በተያያዘም በመድረኩ ላይ የቀድሞው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ጣሰው የቦርድ ሰብሳቢነትን ቦታ ለፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የቀድሞ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክብርት ወ/ሮ ሐና አርአያስላሴ ቦታውን አስረክበዋል።

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ስልጠናው ለዲስትሪክት አመራሮችና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፣ የስልጠና ምስክር ወረቀትም ተበርክቷል። ተሳታፊዎች ያገኙትን እውቀት በየዲስትሪክታቸው በመተግበር አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ በብቃት ለማድረስ ተስማምተዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን በሀገረ አቀፍ ደረጃ ለማስፋፋት የሚያስችለውን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ። 

የስልጠናው ዓላማ የአገልግሎቱን አሰራር፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የደንበኛ አገልግሎት አቅም ማሻሻል ነው። ይህም አገልግሎቱን በሁሉም የፖስታ ቅርንጫፎች በብቃት ለማስፋፋት ይረዳል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለአገልግሎት ማሻሻያ የሚሆኑ ዘመናዊ ላፕቶፖችን ከIOM ተረከበ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ከIOM ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ እና ለቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ማጠናከሪያ የሚውሉ ዘመናዊ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ተረክቧል። የኢትዮጵያ ፖስታን በመወከል

Read More »