ወደ አራዳ ፖስታ ቤት የተዘዋወረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም በይፋ ተመረቀ!

ዛሬ መስከረም 29፣ 2019 ዓ.ም ወደ አራዳ ፖስታ ቤት የተዘዋወረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም በይፋ ተመረቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ላለፉት 50 አመታት በዋናው መስሪያ ቤት ሲገለገልበት የቆየውን የፖስታ ሙዚየም በዘመናዊ መልክ በታደሰው እና በታሪካዊነቱ በሚታወቀው አራዳ ፖስታ ቤት ተዘዋውሮ ዛሬ በይፋ ስራውን ጀምሯል። ይህ ታሪካዊ ሙዚየም የረጅም ጊዜ የፖስታ ታሪካችንን፣ ቴምብሮችን እና ቅርሶችን በውስጡ በመያዝ ለጎብኚዎች ክፍት አድርጓል። መጥተው የፖስታ ጉዟችንን እና ታሪካችንን እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል!

አድራሻ፡ ከአድዋ ሙዚየም ፊት ለፊት አራዳ ፖስታ ቤት

More updates Ethiopost

News

የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ፖስታ የቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያሥላሴ ወደ ታሪካዊው አራዳ ፖስታ ቤት የተዘዋወረውን እንዲሁም በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቆ ሥራ የጀመረውን  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ጎበኙ።

በጉብኝታቸው ወቅት ለ50 ዓመታት በዋናው መሥሪያ ቤት ተጠብቀው ቆይተው በዘመናዊ መልክ የተደራጁ ብርቅዬ ቴምብሮችንና ታሪካዊ የፖስታ ቅርሶችን በመመልከት በአደረጃጀቱ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ በፖስታ እና ሎጅስቲክስ ዘርፍ ላለፉት አምስት ዓመታት ላመጣው የዲጂታል ሽግግር ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር (MInT) የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት!

ዕውቅናው የተገኘው ብሔራዊ መታወቂያን ከአገልግሎቶች ጋር በማስተሳሰር፣ መልእክቶችን በቀጥታ (Real-time) መከታተል የሚያስችል ሥርዓት በመዘርጋት እና አጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ በማዘመን በተመዘገቡ ስኬቶች ነው።

Read More »
News

ለኢትዮጵያ ፖስታ አመራሮችና ሠራተኞች ሲሰጥ የቆየው ባለሁለት ዙር የሞጁላር የግብር ሕግና አሰራር ስልጠና ተጠናቀቀ::

ስልጠናው በተለይም ከቅጥር የሚገኝ ገቢ፣ የወጪ መጋራት እና ሌሎች መሠረታዊ የታክስ አሰራሮች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር እንዲለውጡ ተሳስቧል።

Read More »
News

በUPU እና በኢትዮጵያ ፖስታ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ቀጠናዊ የፖስታ ትራንስፖርት አውደ ጥናት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ 

መድረኩ የአህጉሪቱን የፖስታ እና የኢ-ንግድ ዕቃዎች ትራንስፖርት እንዲሁም የሎጂስቲክስ አቅርቦት ሰንሰለት በማዘመን ረገድ ቀጠናዊ ትብብርን ለማጠናከር አስችሏል።

Read More »