የኢትዮጵያ ፖስታ በአዲስ አበባ ለሚገኘው የመልዕክት ልውውጥ ማዕከሉ ከዓለም አቀፍ ፖስታ ህብረት (UPU) የፖስታ ደህንነት የወርቅ ሰርተፊኬት (Gold Certification) አግኝቷል!
በ2026ቱ የፖስታ ኦፕሬሽንስ ካውንስል (POC) ጉባኤ ላይ የተሰጠው ይህ ዓለም አቀፍ እውቅና፤ ተቋማችን ለላቀ አሰራር እና ለከፍተኛ ዓለም አቀፍ የደህንነት ደረጃዎች ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ማሳያ ነው። በኢትዮጵያ እና በቀሪው ዓለም መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ የንግድ እንዲሁም የመልዕክት ልውውጥን ስናመቻች፤ ዓለም አቀፉን የፖስታ ትስስር ደህንነት መጠበቅ እና የአገልግሎታችንን ታማኝነት ማረጋገጥ ምንጊዜም ቀዳሚ ትኩረታችን ሆኖ ይቀጥላል።
እንኳን ደስ አለን!
አጋሮቻችን እና ባለድርሻ አካላት በኢትዮጵያ ፖስታ ላይ ለምታሳዩት ቀጣይነት ያለው እምነት ከልብ እናመሰግናለን።





