የኢትዮጵያ ፖስታ ለዋናው መሥሪያ ቤት እና ለዲስትሪክት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሲሰጥ የነበረውን በአዲሱ የ”PROPEL” ስትራቴጂ እና በተቋሙ የአሠራር ሂደት መግለጫዎች (SOPs) ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቋል።
የስልጠና መድረኩ ዋና ዓላማ፤ አዲሱን የ”PROPEL” ስትራቴጂ እና የተቋሙን የአሠራር ሂደት መግለጫዎች ወደ ተጨባጭ ተግባር በማሸጋገር፣ የኢትዮጵያ ፖስታን ተቋማዊ አፈጻጸምና ሀገራዊ ፋይዳ ይበልጥ ከፍ ለማድረግ በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ዙሪያ ጠንካራ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ነው።
በዚህም ሁሉም የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከስትራቴጂው ምሰሶዎች ባሻገር የሥራ ክፍሉን የአሠራር ሂደት መግለጫዎች (SOPs) ላይ ሰፋ ያሉ ገለጻዎችን አቀርበዋል፡፡
በመድረኩ ማጠናቀቂያ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያ ፖስታ በ”PROPEL” ስትራቴጂ ዓመታት ውስጥ ሊያሳካቸው ያቀዳቸውን ሁለንተናዊ የለውጥ ግቦች እውን ለማድረግ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅትና እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ በአጽንዖት አሳስበዋል።
ስልጠናው ተቋሙ ለቀጣይ ዓመታት የሚመራበትን የስትራቴጂ ግብ በተቀናጀ እንዲሁም ወጥ በሆነ የአሠራር ሂደት ለማሳካት ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥር ታምኖበታል።











