የኢትዮጵያ ፖስታ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን በሀገረ አቀፍ ደረጃ ለማስፋፋት የሚያስችለውን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ። 

የኢትዮጵያ ፖስታ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘመናዊና ሁሉን አቀፍ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ያቀደውን አዲሱን የውክልና ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን በሀገር አቀፍ ደረጃ በጥራትና በብቃት ለመተግበር በሁሉም ዲስትሪክቶች ለሚገኙ የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች፣ ማኔጀሮች እና ሱፐርቫይዘሮች የሚሰጠውን አጠቃላይ የስልጠና መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል።
 
ይህ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆየው የስልጠና መርሃ-ግብር፤ በዋናነት የአዲሱን የፖስት ፋይናንስ አገልግሎት የአሰራር ስርዓት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ እና የቁጥጥር ደንቦችን በጥልቀት ለማስጨበጥ ያለመ ነው።

ስልጠናው የዲስትሪክት አመራሮችና ባለሙያዎች የሚጠበቅባቸውን የመሪነት ሚና በመወጣት አገልግሎቱን በየአካባቢያቸው በሚገኙ የፖስታ ቅርንጫፎች በስኬት እንዲተገብሩ ከፍተኛ አቅም ይፈጥርላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ ለስልጠናው ታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ስልጠናውን በይፋ ከፍተዋል።

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ስልጠናው ለዲስትሪክት አመራሮችና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፣ የስልጠና ምስክር ወረቀትም ተበርክቷል። ተሳታፊዎች ያገኙትን እውቀት በየዲስትሪክታቸው በመተግበር አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ በብቃት ለማድረስ ተስማምተዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን በሀገረ አቀፍ ደረጃ ለማስፋፋት የሚያስችለውን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ። 

የስልጠናው ዓላማ የአገልግሎቱን አሰራር፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የደንበኛ አገልግሎት አቅም ማሻሻል ነው። ይህም አገልግሎቱን በሁሉም የፖስታ ቅርንጫፎች በብቃት ለማስፋፋት ይረዳል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለአገልግሎት ማሻሻያ የሚሆኑ ዘመናዊ ላፕቶፖችን ከIOM ተረከበ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ከIOM ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ እና ለቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ማጠናከሪያ የሚውሉ ዘመናዊ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ተረክቧል። የኢትዮጵያ ፖስታን በመወከል

Read More »
News

የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ፖስታ የቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያሥላሴ ወደ ታሪካዊው አራዳ ፖስታ ቤት የተዘዋወረውን እንዲሁም በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቆ ሥራ የጀመረውን  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ጎበኙ።

በጉብኝታቸው ወቅት ለ50 ዓመታት በዋናው መሥሪያ ቤት ተጠብቀው ቆይተው በዘመናዊ መልክ የተደራጁ ብርቅዬ ቴምብሮችንና ታሪካዊ የፖስታ ቅርሶችን በመመልከት በአደረጃጀቱ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።

Read More »