የኢትዮጵያ ፖስታ እና ኦሮሚያ ጤና ቢሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ላይ ያተኮረ ስትራቴጂያዊ ውይይት አደረጉ።

የኢትዮጵያ ፖስታ  ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመገናኘት በክልሉ የሚገኙ የጤና ናሙና ሎጂስቲክስ፣ የፋይናንሺያል እና የመልዕክት አገልግሎቶችን በቅንጅት መስጠት ላይ ያተኮረ የትብብር ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሂዷል። የኢትዮጵያ ፖስታ ላለፉት አስር አመታት ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ የመንግስት የጤና ተቋማት የጤና ናሙናዎችን ተቀብሎ ወደ መመርመሪያ ጣቢያዎች በማድረስና ውጤቱንም መልሶ ለጤና ተቋማት በማስረከብ የሎጅስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ይህ አሰራር በናሙና ዝውውር ላይ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በመፍታት ለህብረተሰቡ የጤና ሽፋንን ከመጨመር አንፃር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል።

በኦሮሚያ ጤና ቢሮ ስር ከሚገኙ የዞንና ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች ጋር  የተደረገው ይህ ውይይት የጤና ናሙና ሎጂስቲክስን በቴክኖሎጂ ማዘመንና አጋርነትን ከፍ በማድረግ ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ መሆን ላይ ያተኮረ ነበር። ይህንንም ለመተግበር የኢትዮጵያ ፖስታ በኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሥር በሚገኙ 1440 የጤና ተቋማት ውስጥ የአገልግሎት መስጫ ቦታዎችን ለማግኘት የሚያስችል ስምምነት ላይ ተደርሷል። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ  የኢትዮጵያ ፖስታ የናሙና አሰባሰብ ሂደቱን ለማቀላጠፍ እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጨማሪ አገልግሎቶችን ለመስጠት ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በነዚህ የጤና ተቋማት ውስጥ አገልግሎት መስጫ ጽ/ቤቶችን በማቋቋም አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ላለፉት ተከታታይ አመታት በተሰሩት የሪፎርም ስራዎች ላይ ተመስርቶ ‹‹በጥልቀት እና በስፋት›› በሚል ስትራቴጂክ ፕላን ተቋሙን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ ያለው ስራ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ሙዚየም 50ኛ ዓመት የወርቅ እዩ ቤልዩ ክብረ በዓል!

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ በክብረ በዓሉ ላይ ለተገኙት እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን እንደተቋም የፖስታ ሙዚየሙ ላይ እየተሠሩ ያሉ የማስፋፊያ ሥራዎች እንዳሉ እና በቅርቡ ይፋ እንደሚደረጉ ገልጸዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ የሥራ አመራሮች የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅዶች ላይ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ የአቅርቦት እና ፋሲሊቲ ቺፍ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ጋሻው መርሻ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፤ አያይዘውም በ2017 በጀት ዓመት ለነበረው አፈጻጸም ሁሉም የኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኛ ምስጋና ሊቸረው እንደሚገባ አንስተው በቀጣይም ይኸው የሥራ መነሳሳት እና ተልዕኮዎቻችንን በድል የመወጣት ባሕል ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

Read More »