አበይት ሀገራዊ ክስተቶችን፣ ታላላቅ ስኬቶችን እና ተቋማዊ ጉዞዎችን የሚዘክሩ ሶስት አዳዲስ የቴምብር ስብስቦች በይፋ ወደ ስራ ገብተዋል። አዲሶቹ ታሪካዊ የቴምብር ህትመቶች የሚከተሉት ናቸው፦
1. የ130 ዓመታት ተቋማዊ ጉዞ ኢዮቤልዩ የፖስታ አገልግሎት በኢትዮጵያ የተጓዘበትን የ130 ዓመታት የትስስር፣ የዕድገት እና የዘመናዊነት ታሪክ የሚዘክር ልዩ የመታሰቢያ ህትመት።
2. የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቴምብሮቹ የመጀመሪያ ቀን የህትመት ሽያጭ ባለፈው ቅዳሜ በመላው ሀገሪቱ ተጀምሯል። የኢትዮጵያ ፖስታ ሀገራዊ ግዴታውን በመወጣት የህትመት ወጪውን ሙሉ በሙሉ የሸፈነ ሲሆን፣ በሥዕል ፍሬም የተዘጋጀው ይኸው ቴምብር ለግድቡ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በይፋ ተረክቧል።
3. የሎሬት ዶክተር ጌታቸው ትኩበት መታሰቢያ የተመራማሪው ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ የተመረቁ 4 ልዩ ቴምብሮች ናቸው። ቴምብሮቹ የዶክተሩን የሳይንስና ቴክኖሎጂ የምርምር ማዕከላት፣ በገጠር ነፍሳትን ለመቆጣጠር የተሰሩ ስራዎችን፣ የ”ባዮ ኢኮኖሚክ አፍሪካ” ስኬቶችን እና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በዝርዝር ያሳያሉ።
የእርስዎስ ተቋም ታሪክ በቴምብር ተስንዷል?
አገልግሎቶችን ይበልጥ ለማስፋፋት እና ለማብዛት በተቀመጠው ስትራቴጂ መሰረት፤ ማናቸውም ተቋማት እና ግለሰቦች የራሳቸውን የቴምብር ህትመት ማዘጋጀት የሚችሉበት አሰራር ተዘርግቷል።
የድርጅትዎን ታሪክ፣ የምርት ስም ወይም የባለወለታዎችን ውለታ ለትውልድ እንዲሻገር ለማድረግ፣ የራስዎን ቴምብር አሳትመው ማቅረብ ይችላሉ።












