22ኛው የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በኢትዮጵያ ፖስታ ተከብሯል።

“ትውልድን በስነምግባር ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ቃል 22ኛው የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ አመራሮች እና ሠራተኞች በተገኙበት ተከብሮ ውሏል።

በእለቱ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ በቦታው ተገኝተው ለመላው የዝግጅቱ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው አያይዘውም በተቋሙ ውስጥ ያለ ሁሉም ሠራተኛ የሙስና ተጋላጭነትን በመከላከል እና ብልሹ አሠራሮች ሲታዩ በፍጥነት የእርምት እርምጃዎችን በመውሰድ ተቋማዊ እና ሀገራዊ ግዴታውን እንዲወጣ አሳስበዋል።በመቀጠልም ከእለቱ ጋር በተያያዘ የተዘጋጀው ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል።

በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ ትእግስት በቀለ 22ኛውን የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በማስመልከት የተዘጋጀውን ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ ያቀረቡ ሲሆን በተሳታፊዎች መካከልም የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል።

በመጨረሻም በእለቱ የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሀብት ምዝገባ የተከናወነ ሲሆን በአርአያነት ይህንን ተግባር በመከወናቸው ታላቅ ምስጋና በማቅረብ የዝግጅቱ ፍፃሜ ሆኗል።

More updates Ethiopost

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን የሙዚየም ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተበረከተለት።

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ “የተከፋፈለችውን ዓለም የሚያስተሳስሩ ሙዚየሞች” በሚል እጅግ ወቅታዊ መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ በረከት ዘውዴ እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Read More »
News

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፉ አስመረቀች።

የኢትዮጵያ ፖስታ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ታሪካዊ እሴቶቻችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ይህንን ታላቅ ኩነት አስመልክቶ የወጣው ልዩ የመታሰቢያ ቴምብርም ተቋማችን የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ስኬት ለዓለም በማብሰር ረገድ ያለውን ሚና የሚያጎላ ነው።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ኩባንያ “ልባም” የተሰኘውን የዲጂታል የህይወት መድን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ተሸላሚ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲያረጋግጥ፣ ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

Read More »