የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢት-ስዊች አክሲዮን ማሕበር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢት-ስዊች አክሲዮን ማሕበር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

በስምምነት ፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ እና ኢትስዊች አክሲዮን ማሕበር የተፈራረሙት ስምምነት የኤጀንት ኔትወርክ ማኔጅመንት መተግበሪያን በጋራ ለማበልፀግ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ የተደረሰው ስምምነት እንደተቋም በኢትዮጵያ ፖስታ የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ ፕላን ላይ ትልቅ እመርታን የሚያመጣ መሆኑን ገልፀው በቅርቡ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል። በዝግጂቱ ላይ የኢትስዊች አክሲዮን ማሕበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ይለበስ አዲስም በበኩላቸው ተቋማቸው ከኢትዮጵያ ፖስታ ጋር ይሕን ስምምነት በማድረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው የኦን ላይን ግብይት አከፋፈል ስርአቱን እና የውክልና ባንኪንግ ስራን (agency banking ) በእጅጉ ሊያግዝ የሚችል እንደሚሆን ገልፀዋል።

በተያያዘም ይህን ስምምነት ከታለመለት ግብ ለማድረስ የማስፈጸሚያ ሰነድ ( functional specification document ) በኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮመርሺያል ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ እና በኢትስዊች ቺፍ ፖርቲፎሊኦ ኦፊሰር አቶ አቤኔዘር ላቀው በኩል ተፈርሟል። መጨረሻም በሁለቱም ተቋማት በኩል ለዚህ ስምምነት መሳካት ጥረት ያደረጉ አካላት ምስጋና ተችሯቸዋል።

More updates Ethiopost

News

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በእልባት ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውል ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ፖስታን በመወከል ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር እና  በእልባት ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን በኩል ደግሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ነፃነት ራያ  ተፈራርመዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢት-ስዊች አክሲዮን ማሕበር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

በስምምነት ፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ እና ኢትስዊች አክሲዮን ማሕበር የተፈራረሙት ስምምነት የኤጀንት ኔትወርክ ማኔጅመንት መተግበሪያን በጋራ ለማበልፀግ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ነባር የቦርድ አባላት የሽኝት እና ለአዲሱ ቦርድ አባላት የአቀባበል ስነስርአት ተካሄደ።

በሽኝት ሥነሥርዓቱ ላይ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ የተቋሙ የስትራቴጂ እቅድ ግቡን እንዲመታ የቦርድ አባላቱ ያበረከቱትን ጉልህ አስተዋፅኦ በማንሳት በኢትዮጵያ ፖስታ ውስጥ ትልቁን ታሪክ እንደፃፉ እና ትልቅ ምስጋና እና ክብር እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

Read More »