የኢትዮጵያ ፖስታ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው የዲጂታል ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ወርክሾፕ ላይ ተሳተፈ።
በዚሁ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮመርሻል ኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በቀለ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ዘርፍን ዲጂታላይዝና ዘመናዊ ከማድረግ አኴያ ኢትዮጵያ ፖስታ እየተጫወተ ስላለው ጉልህ ሚና አስረድተዋል። በትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር፣ በአለም አቀፍ የንግድ ማእከል እና #ICTET የተዘጋጀው ወርክሾፕ ፣ የ #AfCFTA (የአፍሪካ ኮንቲኔንታል ነፃ የንግድ ቀጠና) ትግበራን ለመደገፍ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂዎችን ፣የሎጂስቲክስ ሞዴሎችን እና አዳዲስ የመፍትሄ ማሳያ መንገዶች ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነበር።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ብሎም በመላው ዓለም የሚከናወኑ የንግድና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ቀልጣፋ፣ አካታች እና ዘላቂ የሚያደርጉ የሎጂስቲክስ መፍትሄዎችን ለማምጣት የኢትዮጵያ ፖስታ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በወርክሾፑ ላይ ተገልጿል።








