የኢትዮጵያ ፖስታ በኦን ላይን የግብይት ስርዓቱ ላይ በአጭር ግዜ ውስጥ ትልቅ ልዩነትን እየፈጠረ ከሚገኘው ቲና ማርት ጋር አብሮ የመስራት ስምምነት ተፈራርሟል።
በኢትዮጵያ ፖስታ በኩል ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር እና የ ቲና ማርት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኢዘዲን መካከል የተፈረመው ስምምነት አላማ ደንበኞች በቲና ማርት ድረ-ገፅ እንዲሁም ሞባይል መተግበሪያ ገብተው ለሚያዟቸው የመዋቢያ እቃዎች፣ልብሶች እንዲሁም የተለያዩ መገልገያ ቁሳቁሶች በኢትዮጵያ ፖስታ በኩል ያሉበት ድረስ ማድረስ ማስቻል መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ ትእግስት በቀለ የኢትዮጵያ ፖስታ ከጀመረው የዲጂታል ገበያ ትግበራ እንዲሁም ካለው የአመታት የሎጅስቲክስ ልምድ አንፃር ይህ ስምምነት ለደንበኞች የሚቀርቡ አገልግሎቶችን በዘመናዊ ሁኔታ ለማሳለጥ የሚያስችለው መሆኑን ተናግረዋል።
የቲና ማርት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኢዘዲን በበኩላቸው ከ131ዓመታት በላይ ልምድ ባለው በኢትዮጵያ ፖስታ በኩል ትእዛዞች የማድረስ ስራውን በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱ ለድርጅታቸው ታሪካዊ እርምጃ መሆኑን እና ለደንበኞችም ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው እንደሆነ ገልፀዋል።