የአለም ባንክ እና የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ካርዶችን በማተም እና በማሰራጨት ላይ ያለውን የሥራ ሂደት እንዲሁም የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥን በየኢትዮጵያ ፖስታ በመገኘት ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ዜጎች ከየኢትዮጵያ ፖስታ ጋር እንዴት እንደሚገናኙ ከመጀመሪያው የካርድ ህትመት ጥያቄ እስከ መጨረሻ ካርድ አሰባሰብ ድረስ የደንበኞችን ጉዞ ምን እንደሚመስል ቃኝተዋል።
በተጨማሪም ለዜጎች የፋይዳ አገልግሎት ተደራሽነትን ከማስፋፋት አንፃር የኢትዮጵያ ፖስታ አጋርነትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል።