የኢትዮጵያ ፖስታ ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው በ”PROPEL” ስትራቴጂ እና በአሠራር ሂደት መግለጫዎች (SOPs) ላይ ያተኮረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ለዋናው መሥሪያ ቤት እና ለዲስትሪክት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሲሰጥ የነበረውን በአዲሱ የ”PROPEL” ስትራቴጂ እና በተቋሙ የአሠራር ሂደት መግለጫዎች (SOPs) ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቋል።

የስልጠና መድረኩ ዋና ዓላማ፤ አዲሱን የ”PROPEL” ስትራቴጂ እና የተቋሙን የአሠራር ሂደት መግለጫዎች ወደ ተጨባጭ ተግባር በማሸጋገር፣ የኢትዮጵያ ፖስታን ተቋማዊ አፈጻጸምና ሀገራዊ ፋይዳ ይበልጥ ከፍ ለማድረግ በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ዙሪያ ጠንካራ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ነው።

በዚህም ሁሉም የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከስትራቴጂው ምሰሶዎች ባሻገር የሥራ ክፍሉን የአሠራር ሂደት መግለጫዎች (SOPs) ላይ ሰፋ ያሉ ገለጻዎችን አቀርበዋል፡፡

በመድረኩ ማጠናቀቂያ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያ ፖስታ በ”PROPEL” ስትራቴጂ ዓመታት ውስጥ ሊያሳካቸው ያቀዳቸውን ሁለንተናዊ የለውጥ ግቦች እውን ለማድረግ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅትና እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ በአጽንዖት አሳስበዋል።

ስልጠናው ተቋሙ ለቀጣይ ዓመታት የሚመራበትን የስትራቴጂ ግብ በተቀናጀ እንዲሁም ወጥ በሆነ የአሠራር ሂደት ለማሳካት ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥር ታምኖበታል።

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ስልጠናው ለዲስትሪክት አመራሮችና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፣ የስልጠና ምስክር ወረቀትም ተበርክቷል። ተሳታፊዎች ያገኙትን እውቀት በየዲስትሪክታቸው በመተግበር አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ በብቃት ለማድረስ ተስማምተዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን በሀገረ አቀፍ ደረጃ ለማስፋፋት የሚያስችለውን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ። 

የስልጠናው ዓላማ የአገልግሎቱን አሰራር፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የደንበኛ አገልግሎት አቅም ማሻሻል ነው። ይህም አገልግሎቱን በሁሉም የፖስታ ቅርንጫፎች በብቃት ለማስፋፋት ይረዳል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለአገልግሎት ማሻሻያ የሚሆኑ ዘመናዊ ላፕቶፖችን ከIOM ተረከበ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ከIOM ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ እና ለቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ማጠናከሪያ የሚውሉ ዘመናዊ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ተረክቧል። የኢትዮጵያ ፖስታን በመወከል

Read More »