ባለፉት ሶስት ዓመታት የኢትዮጵያ ፖስታን ሲያገለግል በቆየው ቦርድ የተተካው አዲሱ ቦርድ አመራር አባላት በተቋሙ ውስጥ በመገኘት በሁሉም የስራ ክፍሎች ተዘዋውረው ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የአመራር አባላቱን ተቀብለው ሥለተቋሙ የአሰራር ሁኔታ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
በተያያዘም የአዲሱ የቦርድ አባላት በተቋሙ ውስጥ የተመለከቱት የሥራ ሁኔታ በእጅጉ እንዳስደሰታቸው እና በቀጣይ ሊሠሩ ለታሰቡ ሥራዎች የተደላደለ እና መሰረት የጣለ የስራ ከባቢን በመመልከታቸው ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡












