የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንጦጦ በሚገኘው የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ እና የምርምር ማዕከልን ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ በማዕከሉ ጉብኝታቸው ወቅት ባዩት ነገር መደነቃቸውን እና ወደፊት የሳተላይት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሊሰሩ በታቀዱት ስራዎች ላይ ትልቅ እምነት እና ተስፋ እንዳሳደሩም ገልፀዋል።
በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም እንዲሁ በማዕከሉ ጉብኝታቸው መደሰታቸውን ገልጸው ለነገዋ ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ መሠረትነት ጉልህ ሚና የሚጫወት ተቋም በመጎብኘታቸው እና በሥራ አጋርነት አብረው መስራት በመቻላቸው ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ፀሀይ ለተጋባዥ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በጉብኝቱም ወቅት በማዕከሉ ስለሚከናወኑ የምርምር ተግባራትና የሳተላይት መረጃዎችን በመሰብሰብ ለተለያዩ አካላት መረጃዎችን በመስጠት እያበረከተ ስላለው አስተዋፆኦ በዝርዝር ገለጻ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙ የሚታወስ ነው።