የኢትዮጵያ ፖስታ የ2018 በጀት ዓመት አበይት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት

የኢትዮጵያ ፖስታ በ2018 በጀት ዓመት ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የሚከተሉትን ዋና ዋና አፈጻጸሞች አስመዝግቧል፦

✅​ የገቢ ዕድገት፦ ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ከ 3.8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማስገኘት ከ2017 ዓ.ም ጋር ሲነጻጸር የ30% ጭማሪ አሳይቷል።

✅ ​የመልዕክት ብዛት(Traffic) ፦ ከ 6 ሚሊዮን በላይ መልዕክቶች እና እሽጎች የተንቀሳቀሱ ሲሆን፣ 97.2% የሚሆኑት ያለምንም መዘግየት በተያዘላቸው ሰዓት (On-time) መድረስ ችለዋል።

✅ በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፖስታ ከመደበኛ አገልግሎቶች ውጪ ያለው የስራ እንቅስቃሴ መጠን (Non-mail Traffic) ከ 700 ሚሊዮን በላይ ደርሷል!

✅​ የደንበኞች አገልግሎት ማዕከል፦ የጥሪ ማዕከሉ ከ 600,000 በላይ አጠቃላይ የደንበኞች ጥሪዎችን አስተናግዷል።

​በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡት ስኬቶች የነገ መነሻዎች ሲሆኑ፣ በቀጣይ ዓመታት የተቋሙን አገልግሎት አድማስ ይበልጥ ለማስፋት እና የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ አዲስ የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ስራ ተገብቷል።

More updates Ethiopost

News

የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ፖስታ የቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያሥላሴ ወደ ታሪካዊው አራዳ ፖስታ ቤት የተዘዋወረውን እንዲሁም በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቆ ሥራ የጀመረውን  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ጎበኙ።

በጉብኝታቸው ወቅት ለ50 ዓመታት በዋናው መሥሪያ ቤት ተጠብቀው ቆይተው በዘመናዊ መልክ የተደራጁ ብርቅዬ ቴምብሮችንና ታሪካዊ የፖስታ ቅርሶችን በመመልከት በአደረጃጀቱ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ በፖስታ እና ሎጅስቲክስ ዘርፍ ላለፉት አምስት ዓመታት ላመጣው የዲጂታል ሽግግር ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር (MInT) የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት!

ዕውቅናው የተገኘው ብሔራዊ መታወቂያን ከአገልግሎቶች ጋር በማስተሳሰር፣ መልእክቶችን በቀጥታ (Real-time) መከታተል የሚያስችል ሥርዓት በመዘርጋት እና አጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ በማዘመን በተመዘገቡ ስኬቶች ነው።

Read More »
News

ለኢትዮጵያ ፖስታ አመራሮችና ሠራተኞች ሲሰጥ የቆየው ባለሁለት ዙር የሞጁላር የግብር ሕግና አሰራር ስልጠና ተጠናቀቀ::

ስልጠናው በተለይም ከቅጥር የሚገኝ ገቢ፣ የወጪ መጋራት እና ሌሎች መሠረታዊ የታክስ አሰራሮች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር እንዲለውጡ ተሳስቧል።

Read More »
News

በUPU እና በኢትዮጵያ ፖስታ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ቀጠናዊ የፖስታ ትራንስፖርት አውደ ጥናት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ 

መድረኩ የአህጉሪቱን የፖስታ እና የኢ-ንግድ ዕቃዎች ትራንስፖርት እንዲሁም የሎጂስቲክስ አቅርቦት ሰንሰለት በማዘመን ረገድ ቀጠናዊ ትብብርን ለማጠናከር አስችሏል።

Read More »