በኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ እና በኢግልድ የኢንዱስትሪ ዉጤቶች ግዥ እና ሽያጭ ዘርፍ ም/ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባዬ ገዛኸኝ የተፈረመው ይህ አጋርነት የኢግልድ የኢንዱስትሪ ዉጤቶችን በኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፍ ፖስታ ቤቶች በኩል ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና በኦንላይን የኢግልድን የኢንዱስትሪ ዉጤቶች ለሚገበያዩ ደንበኞች በሚመርጡት ቦታ ዕቃዎችን ለማድረስ የሚያስችል ነው::
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፖስታ ተደራሽነቱን ከማስፋት አንፃር የኢግልድን ቅርንጫፍ ቢሮዎች ለሚሰጣቸዉ የተለያዩ አገልግሎቶች በፍራንቻይዝነት መጠቀምን ያካትታል ::

News
የኢትዮጵያ ፖስታ በደንበኞች አገልግሎት ጥራት ተሸላሚ ሆነ።
የአለም አቀፉ የፖስታ ህብረት 28ኛው ጠቅላላ ጉባዬ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ባሳየው የላቀ አፈፃፀም የ2024 የፈጣን መልእክት የደንበኞች አገልግሎት ጥራት ሽልማትን ተቀብሏል።







