ዛሬ የዓለም ፖስታ ቀንን በማስመልከት ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ መሪዎች፣ የድርጅት ደንበኞቻችን እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር “ፖስታ ትላንት፣ ዛሬ እና ነገ” በሚለው መሪ ሐሳብ አክብረናል። ስለ የኢትዮጵያ ፖስታ የ128 ዓመታት ታሪካዊ ትሩፋቶች እንዲሁም በወደፊቷ ኢትዮጵያ ስላለን ቦታ በይነተገናኝ ውይይቶች፣ ገለጻዎች እና ፓነሎች አድርገናል። ጥሪያችንን ተቀብለው ራዕያችንን ለተካፈሉን ሁሉ እናመሰግናለን።
ከእኛ ጋር የዓለም ፖስት ቀንን ላከበሩ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና አመራሮች ታላቅ ምስጋናችንን እናቀርባለን። የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላን ጨምሮ፣ ክብርት ዳግማዊት ሞገስ፣ አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል (የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር) እና ክቡር አቶ ደሳለኝ ወዳጆ ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና ሌሎች በርካታ የመንግስት አመራሮች ተገኝተዋል። ፖስታ ትላንት፣ ዛሬ እና ነገ በሚል መሪ ቃል የምናከብረውን የዓለም ፖስት ቀን እንዲሁም ራዕያችንን ተገኝታችሁ ስለተካፈላችሁን እጅግ እናመሰግናለን!
Today we continued our celebration of #WorldPostDay with high-level government officials, dignitaries, our corporate customers, and relevant stakeholders in line with theme of Post Yesterday, Today, and Tomorrow. We had interactive discussions, presentations, and panels about the 128-years rich historical legacy of Ethiopost as well as our place in the future of Ethiopia. Thank you to all who accepted our invitation and shared in on our vision.
We are thankful to high-level government officials and dignitaries who celebrated #WorldPostDay with us today. Officials including the MINT Minister Dr. Belete Mola who gave the opening remarks, HE Dagimawit Moges, Ato Habtamu H/Micheal (Director General of the Public Enterprise Holdings Administration), and HE Desalegn Wodajo from House of People’s Representative, among many others. Thank you all for sharing our vision for Post Yesterday, Today, and Tomorrow!