የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም National ID Ethiopia አካል የሆነውን የፋይዳ መታወቂያ ካርድ የአቅርቦት አቅምንና ስርዓትን ለማሳደግ የአጋርነት ስምምነቱን የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና የቶፓን ግራቪቲ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ቃልኪዳን አረጋ ዛሬ የፈረሙ ሲሆን ይህ የሥራ ስምምነት ጥራቱን የጠበቀና አስተማማኝ የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ለነዋሪዎች በተቀላጠፈና በዘመነ መልኩ ለማቅረብ የሚያስችል ነው።
በተጨማሪም እያደገ የመጣውን የማህበረሰባችን የፋይዳ መታወቂያ ካርድ ፍላጎት ለማሟላትና ሁሉን አቀፍ እና አካታች የሆነውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዓላማ ለማሳካት የበኩላችንን አስተዋፅዖ ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።