በክቡር አቶ እውነቱ አለነ የተመራ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፖስታ ሁለንተናዊ ተሃድሶ እንዲሁም አጠቃላይ የስራ ክንውን ላይ ውይይት እና የመስክ ጉብኝት አካሂደዋል። በጉብኝታቸውም ወቅት በድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ስለ ድርጅቱ አሁናዊ የስራ ክንውንና በቀጣይ ሊተገበሩ የታቀዱ የሪፎርም ሥራዎች ላይ ሰፊ ገለፃ የቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ ፖስታ ዋናው መስሪያ ቤት የተሰሩ የሕንጻ እድሳት ስራዎችን ፣ የህጻናት ማቆያ ፣ ከጥሪ ማእከል ፣ ከመልእክት መቀበል እስከ እደላ ያሉ የኦፕሬሽን ስራዎችን ከሙያዊ ማብራሪያ ጋር ጎብኝተዋል። ከዋናው መስሪያ ቤት በተጨማሪም በአራት ኪሎ ቅርንጫፍ ፖስታ ቤት በመገኘት የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን እና ሌሎች በቅርንጫፍ ፖስታ ቤቱ የተሰሩ ስራዎችን ጎብኝተዋል።
የአገልግሎቶቻችንን ምህዳር እና ጥራት በማሳደግ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ተጠቃሚነት እየሰራን ባለንበት በዚህ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን እያደረጋችሁልን ስላለው ድጋፍ እናመሰግናለን!