የኢትዮጵያ ፖስታ ሙዚየም 50ኛ ዓመት የወርቅ እዩ ቤልዩ ክብረ በዓል!

በ 1967 ዓ.ም የተቋቋመው ታሪካዊው የፖስታ ሙዚየም 50ኛ ዓመቱን በዛሬው እለት በድምቀት አክብሮ ውሏል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬን ጨምሮ የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እና ታላላቅ የሃገራችን ሰአሊያን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ በክብረ በዓሉ ላይ ለተገኙት እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን እንደተቋም የፖስታ ሙዚየሙ ላይ እየተሠሩ ያሉ የማስፋፊያ ሥራዎች እንዳሉ እና በቅርቡ ይፋ እንደሚደረጉ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም በፖስታ ሙዚየሙ ላይ ሊሠሩ ከታቀዱት የማስፋፊያ ሥራዎች አኳያ የባለድርሻ አካላቱ ሃሳብ እና እገዛ እንደሚያስፈልግ እና በብዙ መልኩ ተቀራርቦ መስራት አስፈላጊነቱ የማያጠያይቅ መሆኑንም ጠቅሰው ለታዳሚው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የፖስታ ሙዚየሙ ሱፐርቫይዘር የሆኑት አቶ ደረጀ ብርሃኑ ለተሳታፊዎቹ በሙዚየሙ ውስጥ ያሉትን 50 ዓመታትን ያስቆጠሩ የቴምብር ሥራዎችን አስጎብኝተው በቅርቡ በካታሎግ መልክ ተዘጋጅተው ለጎብኚዎች እንዲደርሱ ለማድረግ እየተሠራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዚሁ ክብረ በዓል ላይ የተገኙ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ማለትም አቶ አሰፋ ጉያ፣ የሰዓሊ ቦጋለ በላቸው ቤተሰቦች እንዲሁም ሌሎች አንጋፍ አርቲስቶች በመድረኩ ላይ የፖስታ ሙዚየሙ አሁን ላለበት ደረጃ መድረስ በየደረጃው ያሉ የኢትዮጵያ ፖስታ የስራ መሪዎችን አመስግነው ሙዚየሙን ለማዘመን እና ለማስፋፋት በሚደረገው ማንኛውም እንቅስቃሴ ላይ ከኢትዮጵያ ፖስታ ጎን በመቆም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል፡፡

በመጨረሻም የፖስታ ሙዚየሙ የወርቅ እዩ ቤልዩ ክብረ በዓል በቀጣይም ለአንድ ሳምንት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ እንደሚቀጥል እና ጎብኚዎችም መጥተው እየጎበኙ የዚህ ታሪክ ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል፡፡

More updates Ethiopost

News

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በእልባት ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውል ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ፖስታን በመወከል ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር እና  በእልባት ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን በኩል ደግሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ነፃነት ራያ  ተፈራርመዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢት-ስዊች አክሲዮን ማሕበር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

በስምምነት ፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ እና ኢትስዊች አክሲዮን ማሕበር የተፈራረሙት ስምምነት የኤጀንት ኔትወርክ ማኔጅመንት መተግበሪያን በጋራ ለማበልፀግ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ነባር የቦርድ አባላት የሽኝት እና ለአዲሱ ቦርድ አባላት የአቀባበል ስነስርአት ተካሄደ።

በሽኝት ሥነሥርዓቱ ላይ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ የተቋሙ የስትራቴጂ እቅድ ግቡን እንዲመታ የቦርድ አባላቱ ያበረከቱትን ጉልህ አስተዋፅኦ በማንሳት በኢትዮጵያ ፖስታ ውስጥ ትልቁን ታሪክ እንደፃፉ እና ትልቅ ምስጋና እና ክብር እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

Read More »