የኢትዮጵያ ፖስታ የ4ኛ ደረጃ የጥራት እውቅና ሰርተፊኬት ተሸለመ!

ኢትዮጵያ ፖስታ በ13ኛው ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር ላይ ተሳትፎ የ4ኛ ደረጃ የጥራት እውቅና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል። ተቋማችን በዚህ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳትፎ ያስመዘገበው ውጤት እጅግ አበረታች ሲሆን፣ ለጥራት፣ ለተቋማዊ ዕድገትና ለቀጣይነት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ ነው።

ይህንን ስኬት እንደ መነሻ በመውሰድ፣ በቀጣይ ዓመታት የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የጥራት ሽልማት ዋንጫን ለማሸነፍ በትጋት እንሰራለን። ለዚህ አበረታች ውጤት መመዝገብ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የተቋማችን አመራሮች፣ ሠራተኞችና ሁሉም ተሳታፊዎች ልባዊ ምስጋና እያቀረብን ለተገኘው አበረታች ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን!

ለላቀ ጥራትና ለተሻለ አገልግሎት በጋራ እንተጋለን!

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የሩሲያው የኢ-ኮሜርስ ኩባንያ ‘RWB’ ከፍተኛ አመራሮች የገቢና ወጪ ንግዱን ማቀላጠፍ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያዩ፡፡

ቀደም ሲል የተፈረመውን የአጋርነት ስምምነት ተከትሎ በተካሄደው በዚህ ምክክር፣ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያለውን ዓለም አቀፍ የኢ-ኮሜርስ የገቢና ወጪ ንግድ ሂደት ተግዳሮቶች ለመቅረፍና አገልግሎቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ በሚቻልባቸው አሠራሮች ላይ ትኩረት ተደርጓል።

Read More »
News

በቻይና ፖስታ ቢሮ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሊዮ ጂንሮንግ የተመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፖስታ የሥራ ውይይት እና ጉብኝት አደረገ፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ ፖስታ ያለውን ሰፊ መሠረተ ልማትና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያለውን አጋርነት በመጠቀም አዲስ አበባን የምሥራቅ አፍሪካ የኢ-ኮሜርስ ማዕከል ለማድረግና በዲጂታል አሠራርና በአቅም ግንባታ በጋራ ለመሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው በ”PROPEL” ስትራቴጂ እና በአሠራር ሂደት መግለጫዎች (SOPs) ላይ ያተኮረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

መድረኩ ስትራቴጂውንና ወጥ የአሠራር ሂደቶችን ወደ ተጨባጭ ተግባር በማሸጋገር ተቋማዊ አፈጻጸምንና ሀገራዊ ፋይዳን ለማሳደግ የጋራ መግባባት የተፈጠረበት ነው።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ስልጠናው ለዲስትሪክት አመራሮችና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፣ የስልጠና ምስክር ወረቀትም ተበርክቷል። ተሳታፊዎች ያገኙትን እውቀት በየዲስትሪክታቸው በመተግበር አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ በብቃት ለማድረስ ተስማምተዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን በሀገረ አቀፍ ደረጃ ለማስፋፋት የሚያስችለውን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ። 

የስልጠናው ዓላማ የአገልግሎቱን አሰራር፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የደንበኛ አገልግሎት አቅም ማሻሻል ነው። ይህም አገልግሎቱን በሁሉም የፖስታ ቅርንጫፎች በብቃት ለማስፋፋት ይረዳል።

Read More »