አለም አቀፍ የሙዚየም ቀን አከባበርን በማስቀጠል የኢትዮጵያ ፖስታ የታዳጊዎችን የደብዳቤ ፅሁፍ ውድድር የመዝጊያ ዝግጅት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። በውድድሩ ተሳትፈው ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ ታዳጊዎች የኢትዮጵያፖስታ የታብሌት ሽልማት አበርክቷል። ይህ ዝግጅት ተስፋቸውን እና ህልማቸውን የሚገልጹ ወጣት ተሰጥኦዎችን ጊዜ በማይሽረው የደብዳቤ ጽሑፍ ጥበብ አጉልቶ ያሳየ ነበር። “ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ እናግኝ” በሚል ርዕስ የተካሄደው ውድድር ይህን ዘርፈ ብዙ ችግር መፍታት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል።
በዝግጅቱ ላይ ዋና ኮሜርሻል ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በኢትዮጵያ ፖስታ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ ለታዳሚዎች ገለፃ በማድረግ ለፈጠራ እና ለደንበኞች እርካታ ያለንን ቁርጠኝነት አሳይተዋል። በተጨማሪም የፖስታ ሙዚየም ሱፐርቫይዘር አቶ ደረጀ ሁሉንም ታዳሚ የኢትዮጵያፖስታ ሙዚየምን አስጎብኝተዋል።