የኢትዮጵያ ፖስታ በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን በደረሰ የመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ማህበረሰቦች የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር አስተባባሪነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም በመገኘት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ የመሬት ናዳ ለተጎዱ ወገኖች ማቋቋሚያ የሚሆን የ1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በሰው ሃብት ሥራ አመራር ዲፓርትመንት ቺፍ ኢፊሰር በሆኑት አቶ ተሾመ ቢረዳ አስረክበናል፡፡ በአደጋው ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ተጎጂ ቤተሰቦች እና የአካባቢው ማህበረሰብ መፅናናትን እንመኛለን።