የኢትዮጵያ ፖስታ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

የስምምነቱ ዋና አላማ የመንገድ ፈንድ እድሳትን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የአገልግሎት መስጫ ቅርንጫፎች እና በዓመታዊ የተሽከርካሪ ቴክኒክ ደህንነት ምርመራ ተቋማት እንዲኖር ማድረግ ሲሆን ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ቦታ መስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። በመሆኑም የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ቁጥጥር ባለስልጣን የኢትዮጵያ ፖስታ ሕጋዊ ውክል ባለው የመንገድ ፈንድ ሰርተፍኬት እድሳት ስራ ላይ በባለስልጣኑ አገልግሎት መስጫ ቅርንጫፎች በመገኘት ተጨማሪ ደንበኞች አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

ይህ ስምምነት አገልግሎት አሰጣጡንና የመረጃ አያያዝ ስርዓትን በማዘመን የደንበኞችን የአገልግሎት እርካታ እንደሚጨምር የታመነ ሲሆን ጥናትና የአሰራር ማሻሻያ በማካሄድ ዉጤታማ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ብቃት የማረጋገጥ ተልዕኮ  ያለው እንደሆነም በስብሰባው ላይ ተገልጿል፡፡

More updates Ethiopost

News

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በእልባት ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውል ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ፖስታን በመወከል ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር እና  በእልባት ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን በኩል ደግሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ነፃነት ራያ  ተፈራርመዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢት-ስዊች አክሲዮን ማሕበር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

በስምምነት ፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ እና ኢትስዊች አክሲዮን ማሕበር የተፈራረሙት ስምምነት የኤጀንት ኔትወርክ ማኔጅመንት መተግበሪያን በጋራ ለማበልፀግ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ነባር የቦርድ አባላት የሽኝት እና ለአዲሱ ቦርድ አባላት የአቀባበል ስነስርአት ተካሄደ።

በሽኝት ሥነሥርዓቱ ላይ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ የተቋሙ የስትራቴጂ እቅድ ግቡን እንዲመታ የቦርድ አባላቱ ያበረከቱትን ጉልህ አስተዋፅኦ በማንሳት በኢትዮጵያ ፖስታ ውስጥ ትልቁን ታሪክ እንደፃፉ እና ትልቅ ምስጋና እና ክብር እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

Read More »